| Published on:Reporter ( ታኅሣሥ 14፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ግቢ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ለሚገኘው G+4 የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ህንፃ የዳታ ኔትወርክ ሥራዎች እና የህንፃ ጥገና ሥራ በጨረታ አወዳደሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በዘርፉ የተሰማራችሁ ተጫራቾች
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- ለዳታ ኔትወርክ ሥራዎች 3 ሦስት ዓመትና ከዚያም በላይ በኔትወርክ ዝርጋታ ልምድ ያለቸው
- ለሕንፃ ተቋራጮች የንግድ ፈቃድ ደረጃቸው 5 እና ከዚያ በላይ የሆነና በግንባታ ሥራ መልካም የሥራ አፈጻጸም ያላቸው
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ አባል የሆነ
ስለዚህ ከላይ በዝርዝር የቀረቡትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተወዳዳሪዎች ሁሉ ይህ ጨረታ በዚህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በጀትና ሒሳብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 22-23 በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛትና ለጨረታ ማስከበሪያ ሕጋዊነቱ በባንክ በተረጋግጠ ሲፒኦ ብር 50,000.00 (አምሳ ሺህ ብር) በማስያዝ የጨረታ ሰነዱን ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን ጨረታው ታህሳስ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ከረፋዱ 3:00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ስለሆን
ሀ) ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶችን ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፐ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል
ለ) ከላይ በተገለጸው ቀንና ሰዓት ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በጠቅላይ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ በመገኘት የውድድሩን አፈጻጸም መከታተል ይገባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ:- በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጮችን ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆን የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።