| Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 13፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:ጅማ ዞን ጢሮ አፈታ ወረዳ ዲምቱ ከተማ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የጨረታ ማስታወቂያ
በጅማ ዞን የጢሮ አፈታ ወረዳ መንገዶች ባለሥልጣን ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ የሚያከናውነው የተለያዩ መንገድ ጥገና ማሽኖችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ አመልካቾች በሙሉ የወረዳው መንገዶች ባለሥልጣን ጽ/ቤት በሚያወጣው የጨረታ መሥፈርት እና ደንብ መሠረት ወጥታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የማሽኑ አይነት
- ዶዘር CAT D8R
- ግሬደር CAT 140H
- ኤክስካቫተር CAT 330 DL
- ሮለር 16 Ton
- Shower truck 16m3
- ገልባጭ 16m3 ሲሆኑ
አመልካቾች፤
1. ህጋዊ የማሽን ማከራየት ፍቃድ ያላቸው
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢና ቲን ቁጥር ያላቸው
3. የወቅቱን የመንግሥት ግብር የከፈሉና የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ
4 ከሥራ እና ከተማ ልማት የተሰጣቸውን የታደሰ የሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
5. አዳዲስ ማሽኖች ተመራጭነት አላቸው
6. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በወረዳው ገቢዎች ባለሥልጣን ቀርበው የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሀምሣ ብር ) በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የጠቅለላ ዋጋን 2% በክፍያ ማረጋገጫ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8 ተጫራቾች የቅድመ ማጣሪያ ቴክኒካል ዶክመንት በጥንቃቄ በመሙላት እና አስፈላጊ ዶክመንቶችን በማያያዝ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ ሁለቱንም በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ተገቢውን መረጃ በፖስታዎቹ ላይ በጉልህ በመጻፍ ሁለቱንም በሦስተኛ ኤንቨሎፕ ማሸግ እና ቴክኒካል ዶክመንት በማለት መጻፍ ይኖርባቸዋል።
9. የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናንሻል) ዶክመንት ኦርጂናል፣ ፎቶ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሠነድ CPO ለየብቻ በሰም በማሸግ ተገቢውን መረጃ በፖስታዎቹ ላይ በጉልህ በመጻፍ ሦስቱንም በሌላ ኤንቨሎፕ በማድረግ ተገቢውን መረጃ በፖስታዎች ላይ በመጻፍ ሦስቱንም በሌላ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ በመጨረሻም ቴክኒካል እና ፋይናሻል አንድ ላይ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ተፈላጊውን መረጃ በጉልህ ግልጽ በሆነ ጽሁፍ በመጻፍ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 6፡30 ሰዓት ብቻ በወረዳው ገ/ኢ/ት ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
10.ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ በ6፡30 ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ውስጥ በይፋ ይከፈታል።
11. ሥርዝ ድልዝ ያለባቸውንና በግልጽ የማይነበቡ አሻሚ ፊደሎች ያላቸው ሰነዶች ሙሉ ለሙሉ ተቀባይነት የላቸውም።
ማሳሰቢያ-ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጮችን ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ- ጅማ ዞን ጢሮ አፈታ ወረዳ ዲምቱ ከተማ
ለተጨማሪ መረጃ – 047 332 0325 / 0917069793 አሊያም በወረዳው መንገዶች ባለሥልጣን ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በጅማ ዞን የጢሮ አፈታ ወረዳ መንገዶች ባለሥልጣን ጽ/ቤት