| Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 12፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለደሴ ከተማ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 03/2013
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለሥልጣን አገልግሎት የሚውል
- 1ኛ/ በከተማው ውስጥ ፤ለሚያሰራው የመንገድ ስራዎች ኤክስካቫተር ማሽን ባለ ጎማ ኪራይ፣ የኦፕሬተር አበል ወጪ፣ የነዳጅ ወጪ፣የቅባትና ዘይት ወጪ፣ እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን አከራዩ ችሎ በሰዓት ተከራይቶ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- 2ኛ/ የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫ እና ጎማ፣ የህንፃ መሳሪያ፣የሰራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ፣ አላቂ ዕቃ /የጽህፈት መሳሪያ/፣የቢሮ ቋሚ ዕቃ፣ የጽዳት እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- 3ኛ/ የሰራተኞችን ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በእጅ ዋጋ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን፡
1. ተጫራቾች ህጋዊና በዘመኑ የ2013 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ወይም የስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡
3. የግዥ መጠን ከብር 200,000 በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የኤክስካቫተር፣ ማሽን ባለ ጎማ፣ የተሽከርካሪ ማሽነሪ መለዋወጫ እና ጎማ፣ የህንፃ መሳሪያ፣ የስራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ፣ አላቂ እቃ የጽህፈት መሳሪያ፣ የቢሮ ቋሚ እቃ፣ የጽዳት እቃ፣ የሰራተኞችን ደንብ ልብስ የእጅ ዋጋ ማሰፋት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም እቃ ጠቅላላ ዋጋ 2% ከነቫቱ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
7. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ 30 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
8. የመጫረቻ ሰነዱ /የጨረታ ሰነዱ/ ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ለ40 ቀን /አርባ ቀን/ ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
9. የተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ ማለትም ለኤክስካቫተር ማሽን ባለ ጎማ ኪራይ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ለተሽከርካሪ ማሽነሪ መለዋወጫ እና ጎማ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/፣ ለህንፃ መሳሪያ የማይመለስ ብር 100.00 /ኣንድ መቶ ብር/ለሰራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/፣ አላቂ ዕቃ /የጽህፈት መሳሪያ/የቢሮ ቋሚ እቃ፣ የጽዳት እቃ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ የሰራተኞች የደንብ ልብስ የእጅ ዋጋ ማሰፋት የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሣ ብር/ በመክፈል ደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለስልጣን ግዥና ፋ/ንብ/ አስ/የስ/ሂደት ማግኘት ይቻላል፡፡
10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደሴ ከተማ አስ/መንገድ ባለሥልጣን ከግዥና ፋ/ንብ/አስ/የስ/ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሁሉም ጨረታዎች ለተከታታይ 15 ቀን እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል፡፡
11. ጨረታው ለሁሉም እቃዎች የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለሥልጣን መ/ቤት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
12. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ደሴ ከተማ አስ/መንገድ ባለሥልጣን መ/ቤት ድረስ በራሱ ማጓጓዣ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉና ስለጨረታው ዝርዝር መረዳት ከፈለጉ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡- 033 312 91 73/033 311 1041/10 48/10 59 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
15. አድራሻ፡ ካራጉቱ መስጅድ ፊት ለፊት
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለሥልጣን