The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

G+1 ህንጻ ግንባታ እድሳት ሥራ

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 29፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ሆሳዕና
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የጨረታ ማስታወቂያ

በሀድያ ዞን የሆሳዕና ደም ባንክ ለሚያሰራው የG+1 ህንጻ ግንባታ እድሳት ሥራ የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

  1. ደረጃቸው BC/GC-7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን ከደም ባንኩ ግዥ ፋይ/ን/አስተዳደር ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ አስከ 20ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ባለፈቃዱ ወይም ሕጋዊ ተወካዩ አንድ ኮፒ የሰነድ ማስረጃ በመያዝ መግዛት ይችላል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በአሠሪው መ/ቤት ስም 60,000/ስልሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና unconditional bank guarantee letter/ ከፋይናንሻል ሰነድ ጋር ፓስታ በሰም አሽገውና ማህተም በማድረግ ፈርመው ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቶች አስፈላጊውን ዕቃና ሠራተኛ አቅርበው ሥራውን የሚሠሩበትን የፋይናንሻል ኘሮፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶ ግራፊከ ኮፒ የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም አራቱንም ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጐና የፕሮጀክቱን ስም ጠቅሶ የቴክኒካል ፕርፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ ሰነዶች እንዲሁም ኦርጂናል ቴክኒካል ሀሳብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ አራቱንም የቴከኒካል ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጐና ሁለቱንም የቴከኒካል እንዲሁም የፋይናንሻል ፖስታዎች በአንድ ማጠቃለያ እናት ፖስታ በማድረግ የፕሮጀክቱን ስም ጠቅሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶች ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያደርጋል። የአገልግሎት ዋጋው በሰነዱ ላይ በተዘጋጀው ቦታ በአሃዝና በፊደል መሞላት ይኖርባቸዋል። ኦርጂናል የቴክኒካል ሃሣብ የያዘ ሰነድ Bidder Certification of Compliance) ተፈርሞና ታሽጉ መመለስ አለበት፡፡ የቴክኒካል ሃሣብ የያዘውን ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) አለመመለስ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
  4. ጨረታው በ21ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ መኪሎቻቸው በተገኙበት በደም ባንኩ ግዥ ፋይ/ን/አስተዳደር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። 21ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ ደም ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ማሳሰቢያ፡- አዲሱ የተሻሻለው የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የግዥ መመሪያ ተፈጻሚ ይሆናል:: በዞኑ ውስጥ ሶስትና ከዚያ በላይ ስራ ያላቸው ተቋራጮች መሳተፍ አይችሉም::
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 046-555-46-18 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

በሀድያ ዞን ሆሳዕና ደም ባንክ

ሆሳዕና

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page