| Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 29፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር-003/2013
በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ ፋ/ኢ/ል ጽ/ቤት ለወልቂጤ ከተማ አገልግሎት የሚውል ማለትም፡- የዘመናዊ ቄራ ግንባታ ግዢ ለመፈጸም በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ባላቸው ተቋራጮች በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተቋራጮች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡
- 1ኛ/ የዘመኑ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ፡፡
- 2ኛ/ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችልና የዘመኑ የሥራ ግብር የከፈሉ፣ ቲን ነምበር ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማቅረብ የምትችሉ፡፡
- 3ኛ/ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21 ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን፤ በ22ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዛው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቴክኒካል ዶክመንት ይከፈታል፡፡
- 4ኛ/ ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር ብቻ/ አዲስ ክ/ከተማ ከሚገኘው የገቢዎች ቅርንጫፍ ቢሮ በመከፈልና ሪሲቱን በመያዝ ከወልቂጤ ከተማ ፋ/ኢ/ል ጽ/ቤት ግዥ ክፍል ዘወትር በሥራ ሰአት መውሰድ የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- 5ኛ/ ተጫራቾች የጨረታ ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ዶከመንት ሲያቀርቡ ከስር በተገለጸው መሰረት ይሆናል
ሀ/ለቴከኒካል ዶከመንት ኦርጅናልና 2 ፎቶ ኮፒ ለየብቻቸው በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያ የ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከቴክኒካል ኦርጅናል ጋር በማድረግ በእናት ፖስታ አድርጎ በሰም በማሸግ ቴከኒካል በሚል ስመለየት እና ፋይናንሽያል ዶክመንት ኦርጅናልና 2 ፎቶ ኮፒ ለየብቻቸው በማሸግ በእናት ፖስታ አድርጎ በሰም በማሸግ ፋይናንሽያል በሚል በመለየት በ22ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ብቻ ወልቂጤ ከተማ ፋ/ኢ/ል /ፅ/ቤት-ግ/ን/አስ/ዋና/ስ/ሂደት ክፍል ውስጥ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን የሚገባ ሲሆን የቴክኒካል ዶክመንት ጨረታው 4:30 ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
6ኛ/ ከቴከኒካል ግምገማ ወደ ፋይናንሽያል ያለፉተወዳዳሪዎች ፋይናንሽያል ዶክመንት የሚከፈትበት ቀነ ቀጠሮ በተቋሙ በማስታወቂያ ቦርድ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
7ኛ) በBC(ቢሲ) /GC(ጂሲ) ደረጃ 4 እና ከዚህ በላይ ፈቃድ ያላቸው ብቻ መወዳደር የሚችሉ መሆኑ፡፡
8ኛ/ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
9ኛ/መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11/ ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው የእውቅና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- 1/ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ ኮሚቴ ጨረታውን ሊከፍት ይችላል፡፡
- 2/ በአፈጻጸም ምከንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መወዳደር አይችሉም።
- 3/ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የሥራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
- 4/ በጨረታው ሂደት ውስጥ በየትኛውም ግምገማ ተሻሽሎ የወጣው የክልሉ ግዢ መመርያ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ እንገልጻለን፡፡
ለበለጠ መረጃ አድራሻ፡- በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ ል/ጽ/ቤት ብሩክ ህንጻ ፊት ስፌት ቴሌ አጠገብ ከተሠራው አዲሱ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ህንጻ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ወደ ቀኝ ሲታጠፉ የወ/ከ/ፋ/ኢ/ ል/ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0113658187 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡
በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር
የፋ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት