The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

10 ክፍል ያሉት አንድ ብሎክ G+1 የተማሪዎች መማሪያ ክፍል ማስገንባት

Published on:Be’kur ( ኅዳር 7፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጐጃም ዞን የማቻከል ወረዳ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጐጃም ዞን የማቻከል ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በአልማ በጀት በወረዳው ዉስጥ ያለ በወርቅማ ሃሙሲት ቀበሌ አዲስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 10 ክፍል ያሉት አንድ ብሎክ G+1 የተማሪዎች መማሪያ ክፍል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡- ስለዚህ

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን በማቻ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል የተዘጋጀውን የግንባታ ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ::
  3. ሰነዱን በጥንቃቄ ሞልቶ ኮፒና ወርጅናል ሰነዱን በተለያየ ፖስታ በማሸግና በድጋሜ በማጠቃለያ ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን አድራሻ ህጋዊ ማህተም ሙሉ ስምና ፊርማ በመፃፍ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ በ31ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::በዋጋ መሙያዉ ላይ ስርዝ ድልዝ በግልጽ የማይነበብ በፍሉድ የጠፋና እራሱ ተጫራቹ የአስተካከልው ስለመሆኑ ፊርማ/ፓራፍ /የሌለበት ሰነድ ያቀረበ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል::
  4. ተወዳዳሪዎች የሚሰጡት ዋጋ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው
  5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የግንባታ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 140,000.00/አንድ መቶ አርባ ሽህ ብር /ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ/ሲፒኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/unconditional Bank Guarantee/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤታችን የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: ሆኖም ጥሬ ገንዘቡን በፖስታ አሽጎ ማቅረብ አይቻልም::
  6. ተጫራቾች ደረጃ BC/GC-7 እና በላይ መሆን አለባቸው::
  7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
  8. በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት በትክክል ተሞልቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  9. ተጫራቾች የመልካም ስራ አፈፃፅም ማቅረብ የሚችሉ ፣በማንኛውም የግንባታ ስራ ውል ይዘው ያላቋረጡ በውላቸው መሰረት ያጠናቀቁ መሆኑን ከሚመለከተው ህጋዊ አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ::
  10. ጨረታው 31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል::በዚሁ እለት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ ከጠዋቱ በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል::
  11. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0587770480 ደውለው መረጃ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን::

የማቻከል ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page