| Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 6፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የአማካሪ ጨረታ ማስታወቂያ
የየካ ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በተለያዩ ተቋማት ለሚያሰራቸው የለተለያዩ ግንባታዎች የዲዛይን ማሻሻያ የቁጥጥር የማማከር እና የውለታ ማስተዳደር ስራ ለማሰራት በየዘርፉ የተሰማራችሁ የአማካሪ ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
| ሎት | የስራ ዝርዝር | ደረጃ |
| ሎት1 | የወረዳ 12 ኮተቤ ብርሃነ ህይወት ጂ+4 ት/ቤት ግንባታ | 5 እና ከዛ በላይ |
| ሎት 2 | ወረዳ 01 02 እና 06 አስተዳደር ህንፃ ጥገና ስራ | ጥቃቅን ልዩ አማካሪ ደረጃ 1 |
| ሎት 3 | ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ አጥር እና ጥገና ስራ እና ወረዳ 09 የአካባቢ ጥበቃ አጥር ስራ | ጥቃቅን ልዩ አማካሪ ደረጃ 1 |
| ሎት 4 | ወረዳ 06 ስፖርት ሜዳ እና ወረዳ 03 ቤተ-መፅሃፍ አጥር ግንባታ ስራ | ጥቃቅን ልዩ አማካሪ ደረጃ 1 |
- ተጫራቾች ለስራው ህጋዊ ፍቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ምስክር ወረቀት፣ የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር መለያ ቁጥር፣ ከግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እና በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችል የሚያሳይ ከገቢዎችና ጉምሩክ የተሰጠ ሰነድ ያላቸው እና የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ ኦሪጅናል ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በየካ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ከምህንድስና ግዥ ከፍል 4ተኛ ፎቅይህ ማስታወቂያ ከወጣበትጊዜጀምሮ ለተከታታይ አስር የስራ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ዶከመንቱን በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት ዋናውንና ሁለት ፎቶ ኮፒ በተለያዩ በታሸገ ኤንቨሎፖች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የታሸጉትን ኤንቨሎፖች ዋና እና ኮፒ መሆናቸውን ለመለየት Original እና copy በማለት በግልፅ ለይተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአስራ አንደኛው የስራ ቀን በየካ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከግማሽ ሰዓት ቆይታ በኋላ በ 5፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በማጠቃለያ (SUMMARY) ገጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ከየካ/ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ምህንድስና ግዥ ቡድን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን የጠቅላላ ዋጋ 2% የገንዘብ መጠን የያዘ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደተጫራቹ ምርጫ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ የግዥ መመሪያው በሚያዘው መሰረት ለየካ ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ብለው አሰርተው ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማንኛውም በክፍለ ከተማችን ያለ ተጫራች በእጁ ፕሮጀክት ካለው በእጁ ያሉት ፕሮጀክቶች ደረጃ ከ75% መብለጡን የሚገልፅ ደብዳቤ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርበታል።
ማሳሰቢያ፡- አንድ ተጫራች ከአንድ ሰነድ በላይ መውሰድ አይችልም ስልክ ቁጥር 0118932217
የየካ ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት