| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 28፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check It!
የመስኖ ግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
/Construction of small scale Irrigation/
በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ የወረጃርሶ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለወረጃርሶ ወረዳ ግብርና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት ከግብርና እድገት ፕሮግራም(AGP-II) ባገኘው የበጀት ድጋፍ በዳዬ ቱቲ ቀበሌ ገ/ማህበር ውስጥ የመስኖ ግንባታ ስራ ፕሮጀክት በበሪ ወንዝ ላይ /for laga Bari small scale Irrigation up grade construction/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከናወን ይፈልጋል፡፡
- በዚህ ጨረታ ላይ የሚጫረት በዘርፉ የታደሰ ደረጃ/category of invited/ ጠቅላላ የግንባታ ስራ /GWWC/ ወይም በውሃ ግንባታ ስራ /WWC የግንባታ ፍቃድ ያለው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ/ ቫት ተመዝጋቢ ስለመሆኑ እና የዘመኑን ግብር ግዴታውን የተወጣ ስለመሆኑ የሚገልጽ ሰነድ ሊኖረው ይገባል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 21 የስራ ቀናት እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 300/ሦስት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ወረጃርሶ ወረዳ ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12 በአካል በመገኘት መግዛት ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላው ዋጋ አንድ ፐርሰንት /1%/ በCPO ወይም bank guarantee only during submission/ ወረጃርሶ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ማስያዝ ይገባዋል፡፡
- በዚህ ጨረታ ላይ የሚጫረት ቴክኒካል መመዘኛውን /technical evaluation/ ለብቻ ኦሪጅናልና ኮፒውን ለይቶ በሰም በማሸግ እንዲሁም ፋይናንሻል መመዘኛውንም /financial/ evaluation/ ለብቻ ኦሪጅናልና ኮፒውን ለይቶ በሰም በማሸግ፣-Cpo’n ለብቻ በማሸግ በመጨረሻ አምስቱን ኢንቨሎፕ በአንድ ኤንቨሎፕ /mother document/ በሰም አሽጎ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ድረስ ወረጃርሶ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- ጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ22ኛው ስራ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ በ5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ጨረታው በ21ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም በተጠቀሰው ሠዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው ሠዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታው መወዳደሪያ ሙሉ መስፈርት በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ውስጥ ይገኛል፡፡
- ተወዳዳሪዎች የጨረታው ሰነድ ከመሙላታቸው በፊት ፕሮጀክቱ የሚሰራበት ቀበሌው ድረስ በመሄድ የግንባታው ቦታ ማየት አለባቸው፡፡ ለማየታቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0111 870617፣0985376746፣ 0969148899፣ 0947546647፣0910517427 በመደወል ወይም ወረጃርሶ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በአካል ቀርበው መረዳት ይችላሉ፡፡
በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የወረጃርሶ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
/ቀሬጎሃ/