| Published on:Be’kur ( ጥቅምት 23፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ |
Remaining Time for Bid Submission (Check it)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ት/ጽ/ቤት ለዝብቲት የመ/ደ/ት/ቤት አገልግሎት የሚውል አንድ ብሎክ የወንዶች መፀዳጃ ቤት አንድ ብሎክ የሴቶች መፀዳጃ ቤት እና አንድ ብሎክ የሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ክፍል እና ለእኔሣ የመ/ደ/ት/ቤት አንድ ብሎክ የወንዶች መፀዳጃ ቤት አንድ ብሎክ የሴቶች መፀዳጃ ቤት እና አንድ ብሎክ የሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ክፍል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ተጫራቾች፡-
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጥቅል ዋጋ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
- ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የማይመለስ ብር 50.00 ብቻ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 7/3/2013 ዓ.ም 3፡00 ድረስ በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ገገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ፋይናስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው ከተጫራቾች መመሪያ ጋር የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ እቃ በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ በማካተት በእያንዳንዱ ገጽ ፊርማና ማህተም በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ በፖስታው ላይ የድርጅቱን ስም፣ አድራሻ ፣ ፊርማ ፣ ማህተም በማድረግና የጨረታ ማስከበሪያ ለብቻ በማሸግና ሶስቱን ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግና ከላይ የተጠቀሰውን አድራሻ በሙሉ በማጠቃለል ፖስታው ላይ በመጥቀስ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታውን በ8/3/2013 ዓ.ም በ16ኛው ቀን እስከ 3፡00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚችሉና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ታሽጎ በ3፡30 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዮ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ላይ ያላቸውን አስተያየት የጨረታ ቀኑ ከማለቁ 1 ቀን በፊት ለጽ/ቤቱ በስልክም ሆነ በአካል አቤቱታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ አይነት የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 1.5 በመቶ እና በላይ ሆኖ የቫት ተመዝጋቢ ተወዳዳሪዎች ከሆኑ የሚያሲዙት የጨረታ ማስከበሪያ ከነቫቱ መሆኑን እና እንደ ተጫራቾች ምርጫ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒዮ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይንም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ በመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ጥሬ ገንዘቡን በመሂ/1 ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክር ተጫራች ካለ ከጨረታ ውጭ ሆኖ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ብር ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለተጨማሪ መረጃ ቢፈልጉ በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 0586660003 /0586660414/ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር