The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

የዲዛይን ስራዎች

Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 12፣ 2013 )Place of Bid Competitions:አዲስ አበባ
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002D/2013

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራከሽን ቢሮ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች የዲዛይን ስራዎችን የሚሰሩ አማካሪዎችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት

ተጫራቾች ለሥራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ፤ ወቅታዊ ታክስ ክሊራንስ የሚያቀርቡና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ አጭር ምዝገባ ያደረጉና የ2013ዓ.ም ያሳደሱ የአማካሪ ድርጅቶች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ሎት 1 የካ ጣፎ እሳት አደጋ ጂ6 ህንፃ (CAE-1)
  2. ሎት 2 አራዳ አትክልት ተራ ቢ+ጂ+3 ህንፃ (CAE-1)
  3. ሎት 3 ጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ቢጂ+7 (CAE-1 እና በላይ)
  4. ሎት 4 ፈረንሳይ ፖሊስ ጣቢያ ቢ+ጂ+7 (CAE-1 እና በላይ) 
  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ 8ኛ ፎቅ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 18 የስራ ቀናት ድረስ የማይመለስ 200.00(ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመመላትና በሰም በማሸግ የጨረታ መመሪያ በሚያዘው መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ 8ኛ ፎቅ በሚገኘው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት 19ኛው የስራ ቀን ድረስ ባለው ጊዜ እስከ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን (Technical & Financial Proposal ) ለእያንዳንዱ ኣንድ ኦሪጂናልና ሁለት ኮፒ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የቅድመ ብቃት ጨረታ ሰነድ (Technical Proposal ) በዚሁ ዕለት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 801 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው መሰረት በባንክ ክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች ከአንድ ሎት በላይ መወዳደር አይችልም፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች ከኮንስትራክሽን ቢሮ ጋር ፕሮጀክት ካለው በእጁ ያሉት ፕሮጀክቶች ፋይናንሻያል ደረጃው ከ75% መብለጡን የሚገልጽ ማስረጃ ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- የጨረታ መክፈቻው 19ኛ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page