The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሎቤድ ሃይቤድ/ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ከባድ ተሸከርካሪዎችን…

Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 5፣ 2013 )Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Remaining Time for Bid Submission

የሎቤድ /ሃይቤድ/ ተሽከርካሪዎች የትራንስፖርት

ኪራይ አቅርቦት የምዝገባ ጥሪ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሎቤድ ሃይቤድ/ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ከባድ ተሸከርካሪዎችን በተቀመጠው ቁርጥ ዋጋ መሰረት ፍላጎቱ ሲኖር ተከራይቶ በሃገሪቱ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ለሚገኙ የመንገድ፣ የውሃ እና የህንፃ ግንባታ ፕሮጀክቶችና የተለያዩ የኮንስትራክሽን ግብዓቶችና ማሽነሪዎችን የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት እንደየመንገዱ ዓይነትና ባህሪ እና የመሬት አቀማመጥ ተጨባጭ ሁኔታተጠንቶ በተዘጋጀው የኪራይ ዋጋ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የምትፈልጉ አከራዮችእና ትራንስፖርተሮች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ባሉትአስራ አምስት /15/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎችኮርፖሬሽን ቃሊቲ በሚገኘው ኮንስት/ መሣሪ/ማሽነ/ማኔጅ/ዘርፍ የማሽነሪ ኪራይ ክፍል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በምዝገባው ለመሳተፍ የሚከተሉትንመስፈርቶች ማሟላት የሚኖርባቸው መሆኑን እንገለፃለን፡፡

  1.  አከራዮች ትራንስፖርተሮች በምዝገባው ለመሳተፍ የሚችሉት በግል ንብረታቸው ወይምህጋዊ ውክልና ማቅረብ በሚችሉባቸው ተሽከርካሪዎች ብቻ ነው፡፡
  2. አከራዮች /ትራንስፖርተሮች በኮርፖሬሽኑ ስር ለሚተዳደሩ ፕሮጀክቶች ለመሰማራትፍላጎት ያላቸው ብቻ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡
  3. አከራዮች ትራንስፖርተሮች ለምዝገባው የሚያቀርቧቸው ተሽከርካሪዎች በጥሩ ይዞታ |ያሉ መሆን አለባቸው፡፡
  4. አከራዮች/ትራንስፖርተሮች በአቅራቢዎች ዝርዝር ስለመመዝገባቸው የሚያስረዳ ሠርተፊኬት ለምዝገባ ሲቀርቡ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. በምዝገባው ለመካፈል የሚፈልጉ አከራዮች/ ትራንስፖርተሮች በተራ ቁጥር 5 ከተጠቀሰው በተጨማሪ የዘመኑን ግብር የተከፈለበትንና ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደበ2012 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ በምዝገባው ለመሳተፍ ከገቢዎች ባለሥልጣን የተሰጠየድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. አከራዮች/ ትራንስፖርተሮች የሚያቀርቧቸው ተሽከርካሪዎች የመድን ዋስትና የተገባላቸውመሆን አለባቸው፡፡

የአከራዮች/ትራንስፖርተሮች ምዝገባ አካሄድ፡

  1.  ምዝገባ የሚካሄደው በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቃሊቲ በሚገኘው ኮንስት/መሣሪ/ማሽነ/ማኔጅ/ዘርፍ የኪራይ መሳሪያ አስተዳደር ቡድን ቡድንነው፡፡
  2. የተሽከርካሪዎች የመጫን አቅም ከተሽከርካሪው አምራች ድርጅት የተሰጠ ማረጋገጫተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  3. አከራዮች ትራንስፖርተሮች ይህ ማስታወቂያ ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ለምዝገባየሚያስፈልገውን መረጃ በመያዝ በአካል ቀርበው መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡
  4. የአከራዮች የትራንስፖርተሮች ምዝገባ የሚካሄደው በተሽከርካሪው የመጫን አቅምናአከራዩ የስምሪት ፍላጎት ፕሮጀክቱ ተለይቶ ይሆናል፡፡
  5. አከራዮች በጊዜ ገደቡ ውስጥ ለመመዝገባቸው በምዝገባ ሰነዱ ላይ በስማቸውአንፃር መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡
ተ.ቁየፕሮጀክቱ ስም ከአዲስ አበባ ያለው ርቀት
 አስፋልት ጠጠር
1ቃሊቲ ዕቃ ግ/ቤት  
2የአላባ- አንጋጫ-ዋቶ መን/ግ/ፕ/ት  
3ከሰም የዋና ቦይ ጥገና ፕሮጀክት302 
4የወልቂጤ ከተማ መ/ግ/ፕ እና ሰበታ-ቆሬ ከ/መ/ጥ/ፕ158 
5(አለምገና-ቡታጅራ-ሆሳና፣ አረካ ከ/መ/ጥ/ፕ፣150 
6[አዳማ -አዋሽ-ሚሌ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት1270
7አዲስ-አዳማ-አሰላ መ/ግ/ፕ/ት175 
8ዱለቻ- አዋሽ አርባ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት2500
9አዋሽ-ሚሌ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት3830
10ሞጆ ደረቅ ወደብ ግንባታ ፕሮጀክት800
11ጊዳቦ ግድብና ካናል ግንባታ ፕሮጀክት3800
12ዲማ ራድ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት7000
13ኮንግ -በጎንዲ-ወንበራ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት750 
14አርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት መስኖ ግንባታ ፕሮጀክት380 
15ጉደር ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት1750
16ርብ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት686 
17መገጭ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት7330
18ግሸን-መገንጠያ መ/ግ/ፕ/ት480 
19ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት118525
20ኩራዝ ግድብ፣ካናል እና መንገድ ግ/ፕሮጀክቶች960 
21ጅንካ መንደር መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት883 
22የሳላይሽ-ኦሞ መ/ግ/ፕ  
23ያቤሎ ባይ-ፓስ መ/ግ/ፕሮጀክት፣ፕ/ት600 
24ሰመራ ዩኒቨርሲቲ መጠጥ ውሃ ግ/ፕ፣ ተንዳሆ እርሻ595 
25አክሱም-ሽሬ ከ/ጥ/ፕ1041 
26ካዛ ግ/ግ/ፕ  
27ተንዳሆ የዋና ቦይ ጥገና እና የተንዳሆ እርሻ ሥራ600 
28ሚሌ-ጋላፊ፡ዲቸቶ መገንጠያ መ/ሥ/ፕ680 

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page