The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

ጂ 4 መዋቅርና የግንባታ ማስፈፀሚያ ስራ

Published on: Addis Zemen ( መስከረም 28፣ 2013 ) /Place of Bid Competitions:አዲስ አበባ

Remaining Time for Bid Submission

የግንባታ ስራ ተቋራጮች ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር con/004/2013

በልደታ/ክ/ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በወረዳ 2 ክልል ውስጥ ለሚያሰራው የG+4 መዋቅርና የግንባታ ማስፈፀሚያ ስራ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ብቃት ያላቸው የስራ ተቋራጮች አወዳድሮ ማሰራትስለሚፈልግ በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ የግንባታ የስራ ተቋራጮች ለስራው አስፈላጊ የሆኑ የተሟላ የሰው ሃይል ፤ በኮንስትራከሽን ዘርፍ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ማቅረብ የሚችሉ እና በተጨማሪምከታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

ሎትየፕሮጀክቱ ስም

የሚገኙት

ወረዳ
የስራ

ተቋራጮች

ደረጃ
የጨረታ ሰነድ መሽጥ

የሚጀምርበት ቀን
ጨረታው

የሚገባበት ቀን
ጨረታው

የሚከፈትበትን ቀን፤ ሰዓት እና ቦታ
1የመዝገበ ብርሃን ት/ቤት

ጂ 4 መዋቅርና የግንባታ

ማስፈፀሚያ ስራ
2GC/BC 4 እናከዚያ በላይ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀንጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት

16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት

እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ


ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት በ16ኛው ቀን ጠዋት

4፡30 ሰዓት በከ/ከተማው አዳራሽ 3ኛ ፎቅ

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

  1.  በስራ ዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የታደሰ የፌደራል የብቃት ማረጋገጫ ወይም የአዲስ አበባ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፍቃድያላቸው፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፤ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
  2. ከመንግስት ግዥ ንብረት ማስወገጃ ኤጀንሲ (የአቅራቢነት) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድጨረታውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ሰነድ የማይመለስ ብር 300(ሶስት መቶ) በመከፈል በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ህንጻ አራተኛ ፎቅኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በምህንድስና ግዥ ቡድን ከፍል በመምጣት ሰነዱን በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የወሰዱትን ሰነድ ሲመለሱ የቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጂናል ከሁለት ኮፒ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ የታሸገውን ሶስት ኤንቨሎፕ በአንድ እናት ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ እና የፋይናንሻል ሰነድአንድ ኦርጂናል ከሁለት ኮፒ ጋር በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ የታሸገውን ሶስት ኤንቨሌፕ በአንድ እናት ኤንቨሎፕ በሰም አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም እያንዳንዱ ሰነድና ኤንቨሎፕ ላይፊርማና ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ዋጋ (rate) ያልተሞላበት የስራ ዝርዝር እንዲሁም የስራ ዝርዝር ዋጋ (rate) ላይ ድልዝ ስርዝ እና ፍሉድ መጠቀም ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
  6. ተጫራቾች ለመወዳደር ላቀረቡት ዋጋ ሁለት ፐርሰንት (2%) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (bid bond or bid security) ወይም በባንክ ትዕዛዝ ሲፒኦ (cpo) በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና(UNCONDIONAL BANK GUARANTEE) ከታወቀ ባንክ በልደታ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ስም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በልደታ ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. . ጨረታው በተጠቀሰው ቀን፤ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  9. አሰሪው መስሪያ ቤት አሸናፊው ካሸነፈበት አጠቃላይ ስራ 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፡
  10. በተጨማሪም የትኛውም ከላይ የተዘረዘሩትን ሆነ በጨረታው ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ህጎች አለማክበር በሚያስገቡት የጨረታ ሰነዶቻቸው በሁሉም ገፆች ላይ ማህተምና ፊርማአለማድረግ ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • አድራሻ፡- ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ስፌት ልደታ ክፍስ ከተማ አስተዳደር ህንጻ አራተኛ ፎቅ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን ክፍል

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page