The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

የተለያዩ ግንባታዎች ግንባታ ሥራ

Published on: Addis Zemen ( ጳጉሜ 5፣ 2012 ) /Place of Bid Competitions:አዲስ አበባ 

Remaining Time for Bid Submission

የጨረታ ማስታወቂያ 

የየካ ክ/ከተማ ኮንስትራከሽን ጽ/ቤት በተለያዩ ተቋማት ለሚያሰራቸው የተለያዩ ግንባታዎች ግንባታ ሥራ ለማሰራት በየዘርፉ የተሰማራችሁ የኮንስትራክሽን ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ 

ሎትየሥራ ዝርዝርደረጃ
ሎት 1ወረዳ 13 መሪ ህዳሴ አፀደ ሕፃናት ጂ+0 እና ጂ+1 ግንባታ4 እና ከዚያ በላይ
ሎት2ወረዳ 14 ኣባዶ ኮንዶሚኒየም አፀደ ሕፃናት ጂ+0 እና ጂ+ ግንባታ4 እና ከዚያ በላይ
ሎት3ወረዳ 06 ሚስፎርድ ጂ+4 ግንባታ4 እና ከዚያ በላይ
ሎት4ወረዳ 09 አጥር የጥበቃ ቤት እና የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ5 እና ከዚያ በላይ
ሎት5ወረዳ 13 ስፖርት ሜዳ ግንባታ5 እና ከዚያ በላይ
ሎት6ወረዳ 14 ስፖርት ሜዳ ግንባታ5 እና ከዚያ በላይ
ሎት7ወረዳ 06 ጤና ጣቢያ እድሳት እና ጂ+0 ፋርማሲ ግንባታ5 እና ከዚያ በላይ
ሎት8ወረዳ 09 ጂ+1 ወጣት ማእከል እድሳት6 እና ከዚያ በላይ
ሎት9ወረዳ 12ጂ+1 ወጣት ማእከል እድሳት6 እና ከዚያ በላይ
ሎት10ወረዳ 09 ጂ+3 ወጣት ማእከል እድሳት6 እና ከዚያ በላይ
ሎት11ወረዳ 10 ጤና ጣቢያ እድሳት6 እና ከዚያ በላይ
ሎት12ወረዳ 1 3በ1ስፖርት ሜዳ ግንባታ6 እና ከዚያ በላይ
ሎት13ወረዳ 13 ጣፎ ት/ቤት አጥር ሥራ6 እና ከዚያ በላይ
ሎት14ወረዳ 13 ወጣት ማእከል እድሳት6 እና ከዚያ በላይ
ሎት15ወረዳ 01 ካርድ እና ቲቢ ክፍል ግንባታ6 እና ከዚያ በላይ
ሎት16ወረዳ 02 ሕፃናት ማቆያ እና ቤተሰብ አገልግሎት ግንባታ6 እና ከዚያ በላይ
ሎት17ወረዳ 02 3በ1 ስፖርት ሜዳ ግንባታ6 እና ከዚያ በላይ
ሎት18ወረዳ 04 ወጣት ማእከል እድሳት እና አጥር ሥራ6 እና ከዚያ በላይ
ሎት19ወረዳ 06 ወጣት ማእከል እድሳት6 እና ከዚያ በላይ
ሎት20ወረዳ 08 ወጣት ማእከል እድሳት6 እና ከዚያ በላይ
ሎት21ወረዳ 05 ኮከበ ፅባህ ት/ቤት አጥር ሥራ6 እና ከዚያ በላይ
ሎት22ወረዳ 13 አያት ት/ቤት ኤሌክትሪክ ሥራ8 እና ከዚያ በላይ በዘርፉ የተደራጁ
  1. ተጫራቾች ለሥራው ሕጋዊ ፍቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የምዝገባ ምስክር ወረቀት የአቅራቢነት ምዝገባና የታከስ ሠረተፍኬት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ማስረጃ ሰርተፍኬት ያላቸው እና የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ ኦሪጅናል ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡ 
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በየካ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ከምህንድስና ግዥ ክፍል 4ተኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት የሥራ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡ 
  3. ከሎት 1-7 ላሉት ሥራዎች ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ዶክመንቶቹን በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት ዋናውንና ሁለት ፎቶ ኮፒ በተለያዩ በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የታሸጉትን ኤንቨሎፖች ዋና እና ኮፒ መሆናቸውን ለመለየት Original እና Copy በማለት በግልፅ ለይተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
  4. ከሎት 8-22 ላሉት ሥራዎች ፋይናንሺያል ዶክመንቶቹን ብቻ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት ዋናውንና ሁለት ፎቶ ኮፒ በተለያዩ በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የታሸጉትን ኤንቨሎፖች ዋና እና ኮፒ መሆናቸውን ለመለየት Original እና Copy በማለት በግልፅ ለይተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
  5. ሎት 8-22 ላሉ ሥራዎች ጨረታው በአስራ ስድስተኛው ቀን በየካ ክፍለ ከተማ ግራውንድ ላይ የሚገኘው ትልቁ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከግማሽ ሰዓት ቆይታ በኋላ 5፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ 
  6. ከሎት 1-7 ላሉ ሥራዎች ጨረታው በአስራ ሰባተኛው ቀን በየካ ክፍለ ከተማ ግራውንድ ላይ የሚገኘው ትልቁ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከግማሽ ሰዓት ቆይታ በኋላ በ5፡00 ሰዓት ላይ የቴክኒክ ሰነዱ ይከፈታል፡፡ 
  7. ተጫራቾች በማጠቃለያ (SUMMARY) ገጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡ 
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሎት-ሎት7 ላሉ ሥራዎች የማይመለስ ብር 200 እና ከሎት8- ሎት21 ላሉ ሥራዎች የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ከየካ/ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ምህንድስና ግዥ ቡድን መውሰድ ይችላሉ፡፡ 
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% የገንዘብ መጠን የያዘ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደተጫራቹ ምርጫ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የመድን ዋስትና የግዥ መመሪያው በሚያዘው መሠረት ለየካ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ብለው አሰርተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
  10. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
  • ማሳሰቢያ፡- አንድ ተጫራች ከአንድ ሰነድ በላይ መውሰድ አይችልም፡፡ 
  • ስልክ ቁጥር፡- 08-93-22-17 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የየካ ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት  

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page