The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

በክልል ጤና ቢሮ በጀት በዴቻ ወረዳ ተጀምሮ የተቋረጠውን የቀሺ ጤና ጣቢያ ቀሪ ስራዎች…

Published on:Addis Zemen ( ጳጉሜ 5፣ 2012 ) /Place of Bid Competitions:ደ/ብ/ብ/ሕ/ክ መንግስት የካፋ ዞን

Remaining Time for Bid Submission

የጨረታ ማስታወቂያ 

የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ከካፋ ዞን ጤና መምሪያ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት በክልል ጤና ቢሮ በጀት በዴቻ ወረዳ ተጀምሮ የተቋረጠውን የቀሺ ጤና ጣቢያ ቀሪ ስራዎች ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ 

ስስዚህ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ :

  • የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣የቲን/TገN/ እና የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ኦርጅናል እና አንድ የማይመለስ ኮፒ ዶክመንት ሰነድ ሊገዙ ሲመጠኑ ይዘው ቀርበው እንዲመሳከር ሳያደርጉ ሰነድ መግዛት አይችሉም::
  • ተጫራቾች ደረጃ BC/GC-5 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርባቸዋል::
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300/ሶስት መቶ ብር/ ካፉ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ቀርበው በመከፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ለተከታታይ 21 ቀናት ካፉ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብ/ አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረበ መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ 100,000 | አንድ መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ CPO (Certified payment order) በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ ስም በማሰራት ከኦርጅናል ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  • ተጫራቶች ፋይናንሻል እና ቴክኒካል የጨረታ ዶክመንት ተገቢውን ፊርማ እና ማህተም በማሳረፍ ለየብቻ አንድ አንድ ኦርጅናል እና ሦስት ሦስት ኮፒ የተሟላ ሰነድ በሰም/በሙጫ/በታሸጉ ፖስታዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ተከታታይ ቀናት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ንብ/አስ/ በመቅረብ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ:: የጨረታው ሳጥን በ22ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራቀን ይሆናል:: ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ፣ የእቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት የቲን TIN እና የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ኮፒ ዶክመንት ከቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶች ጋር አያይዘው የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  • የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን የመክፈት ሂደት አያስተጓጉልም::
  • ተጫራቾች ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ /performance bond/ ለማስያዝ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው፡፡ 
  • ለአሽናፊው ድርጅት ክፍያው ሙሉ በሙሉ በክልሉ ጤና ቢሮ በጀት የሚሸፈን ይሆናል።
  • ተጫራቾች አሰሪው መ/ቤት ያዘጋጀውን የቴክኒካል ዶክመንት መጠይቅ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል። 
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በመሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 3 311826 መጠየቅ ይቻላል!! 

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ መንግስት የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቦንጋ 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page