Free
| Invited Grade or Category | ጂሲ/ቢሲ -3 እና ከዚያ በላይ |
| Place of competition | አዲስ አበባ |
| Remaining time for BID submission |
የግንባታ ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/13/2013
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል በከፋ ዞን በቦንጋ ከተማ በከፈተው አዲስ የቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ግቢ ቢሮዎች ፤ መጋዝኖች እና የተለያዩ የግንባታ ሥራዎችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ቴክኒካል መስፈርት መሰረት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል:: በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፣
- ደረጃቸው ጂሲ/ቢሲ -3 እና ከዚያ በላይ የሆነ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ እና ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ እንዲሁም ከገቢዎች ሚ/ር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ ኢማ አጠገብ የቀድሞው እርሻ መሣሪያዎችና ቴክኒክ አገልግሎት ኢሚ ግቢ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 110 ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 600.00(ስድስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ 2% በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (unconditiona) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ዋስትናው ለብቻው በአንድ ፖስታ ውስጥ ተደርጎ ከኦርጂናል ቴክኒካል ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የጨረታው ዋጋ ለ60 ቀናት የጸና ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ዶክመንት መሰረት ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል በተለያዩ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም ፋይናንሽያል ሰነዱን ዋና እና ኮፒ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ሚያዝያ 14 ቀን 2010 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
- ስልክ ቁጥር፡- 0114420797/0114-70 90 95/0114-42 36 08
- ፋክስ፡- 0114-421312 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
Good Luck!