Free
Published Date : Aug 07, 2022
ግልፅ የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያቾን ስካይ ስታንዳርድ ቢዝነስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በኦሮሚያ ክልል ለገጣፎ ከተማ አስተዳደር አንድ ዘመናዊ መጋዘን ለመገንባት በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው የሥራ ዝርዝር መሰረት በግልፅ ጨረታ ደረጃ አራት እና ከዚያ በላይ የሆኑትን የግንባታ ባለሙያዎችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራጮች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) ብቻ በመክፈል ከኩባንያው ዋና ቢሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመግዛት በተጫራቾች መመሪያ ላይ በተገለፀውና በተያያዘው የሥራ ዝርዝር መሠረት የመጫረቻ ሰነዳችውን አዘጋጅታችሁ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 የሥራ ቀናት ውስጥ በኩባንያው ቢሮ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ።
ጨረታ ነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ከረፋዱ 5 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከሰዓት በ9፡00 ሰዓት ላይ የቴክኒክ ዶክመንቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የቴክኒክ ሰነዱ ላይ አስፈላጊ ግምገማ ከተከናወነ በኃላ የፋይናንሻል ሰነድ የሚከፈትበት ቀን በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለፅ ይሆናል።
ተጫራቾች:_
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልፅ ታክስ ክሊራንስ (Tax Clearance) ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ።
- በተጫራቾች መመሪያ ላይ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ የሚችሉ!
- የሚጫረቱበትን ዋጋ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም፤ የተወካይ ሙሉ ስምና ፊርማ እንዲሁም አድራሻቸውን በመግለፅ በመመሪያው ላይ በተገለፀው መልኩ በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በዘርፉ በቂ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ
- የቴክኒካልና የፋይናንሻል መጫረቻ ሰነዶች ለየብቻ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ሲገኙ ብር አምስት ሚሊዮን ቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የመልካም ሥራ ዋስትና “unconditional Bank Guarantee” ማቅረብ ይገባቸዋል።
- ኩባንያው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድሪሻ፡- ባምቢስ መካነ ኢየሱስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቀጥር 206.
- ስ.ቁ 0911 25 98 84 ወይም 0115 54 92 15